ስክሪንሾት ማስረጃ አይደለም። ስካን ያድርጉት፣ ደንበኛው ከመሄዱ በፊት ገንዘቡ በእርግጥ መግባቱን በሰከንዶች ይወቁ።
ሠራተኞችዎ የሚያደርጉት እያንዳንዱ ማረጋገጫ በአንድ ዝርዝር ውስጥ ይገባል፦ ማን ስካን እንዳደረገ፣ ስንት እንደሆነ፣ በስንት ሰዓት እና ገንዘቡ በእርግጥ መግባቱን። ድምሩ የሚቆጥረው የተከፈለውን ገንዘብ ብቻ ነው።
ሠራተኞችዎን በስልክ ቁጥር ያስገቡ፣ የCBE እና Telebirr አካውንቶችዎን አንድ ጊዜ ያስገቡ። ዝግጅቱ ይኸው ነው።
አይችልም። በፎቶው አንመራም። በደረሰኙ ላይ ያለውን መለያ ቁጥር ወስደን ከባንኩ ጋር እናረጋግጣለን። ባንኩ መዝገብ ከሌለው አልተከፈለም ተብሎ ይታያል።
አይቻልም። አፑ ያረጋገጠውን እያንዳንዱን ደረሰኝ ያስታውሳል። ያንኑ እንደገና ቢያሳዩ ቀይ ሆኖ ይመጣል፦ ቀድሞ ተጠቅመውበታል።
አረንጓዴ ሆኖ ተከፍሏል ተብሎ ይታያል፤ ትርፉም እንደ ቲፕ ይመዘገባል።
ለጊዜው CBE እና Telebirr።
አያስፈልግም። በስልኩ ብራውዘር ላይ ይሰራል፣ የሚወርድ ነገር የለም፣ እንደገቡም ይቆያል።
አዎ። ድረ-ገጹን በስልኩ ይክፈቱና Install ወይም Add to Home screen ይንኩ። ከዚያ እንደ ማንኛውም አፕ ይከፈታል።
አፑ "ገና ማረጋገጥ አልተቻለም" ይላል፣ ሠራተኞችዎም እንደገና መሞከር ይችላሉ። ባንኩ ካላረጋገጠ በስተቀር ተከፍሏል ብሎ አያሳይም።
የCBE እና Telebirr አካውንቶችዎን አንድ ጊዜ ያስገባሉ። ወደ ሌላ ቦታ የተላከ ክፍያ "የተሳሳተ አካውንት" ተብሎ ይታያል።
አንይዝም። ገንዘቡ እንደ አሁኑ በቀጥታ ወደ አካውንትዎ ይገባል። እኛ መግባቱን ብቻ እናረጋግጣለን።
ሌላ ጥያቄ አለ? በTelegram ይጻፉልን።
ወደ እርስዎ መጥተን እናዘጋጃለን፣ ለሠራተኞችዎ እንዴት እንደሚሰራ እናሳያለን። ለመጀመሪያው ወር ምንም ክፍያ የለም።
ለአንድ ወር በነፃ ይሞክሩ ይደውሉ +251 90 505 4616